Telegram Group Search
"ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ....."

(አባ ሕርያቆስ - ቅዳሴ ማርያም)
"የማርን ጥፍጥና ማርን ቀምሶ ለማያውቅ ሰው በመቅመስ እንጂ በቃላት ማስተማር እንደማይቻል ሁሉ የእግዚአብሔርን መልካምነት በቃላት በጠራ መልኩ ማስተማር አይቻልም። ራሣችን ወደ እግዚአብሔር መልካምነት ዘልቀን መግባት ይኖርብናል እንጂ።"

ቅዱስ ባስልዮስ ታላቁ
#የትሩፋት_ሥራ_ጀምር

ጨክነህ ቆርጠህ የትሩፋትን ሥራ ጀምር፡፡ በትሩፋት አጠገብ እየተጠራጠርህ አትኑር፡፡ ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ከማመን ተስፋ ወጥተህ በልብህ እንኳ አትጠራጠር፡፡ ትሩፋትህ ረብህ ጥቅም የሌለው እንዳይሆን የትሩፋት ሥራ ክቡድ አይምሰልህ፡፡ መሐሪ እግዚአብሔር ለለመኑት ሰዎች ጸጋውን ፈጽሞ እንዲሰጣቸው እመን እንጂ ስጦታው እንደየሥራችን አይደለም፡፡ በትጋታችን፣ በማመናችንና በመሻታችን መጠን ነው እንጂ እንደ ሃይማኖትህ ይደረግልህ ብሏልና፡፡

የትሩፋት ሥራም ይህች ናት፣ አንዱ መተምተሚያ አዘጋጅቶ መሐል ራሱን ይተመትመዋል፡፡ በየጊዜው በሚጸልየው ጸሎት እንዳያፍር ትቀርበኛለች ብሎ ያዝናል፡፡ አንዱ አብዝቶ ይሰግዳል፣ ልጸልይ ያለውን ይጸልያል፣ ስለ ጸሎቱ ፈንታ ብዙ ያለቅሳል፣ በልቅሶው ረብህ ጥቅም ያገኝበታል፡፡ አንዱ የልቡና ሥራ የምትሆን ትሩፋትን በመዘከር ይጋደላል፣ ወደ ተወሰነለት ጸጋ ይደርሳል፣ አንዱ ምግብ ነስቶ ሰውነቱን በረኃብ ያስጨንቃታል ጸሎቱን መፈጸም የማይቻለው እስኪሆን ድረስ፣ አንዱ ተናዶ እየመላለሰ ዳዊት ይጸልያል። በመድገም ዘወትር ጸሎትን ገንዘብ ያደርጋታል፣ አንዱ መጽሐፍ ለመመልከት፣ ለመድገም ጽሙድ ሆኖ ይኖራል፣ አንዱ ከአምላክ በተገኙ መጻሕፍት ያለውን ትርጓሜ ምሥጢር ያስበዋል፣ ያስተውለዋል፣ ይመረምረዋል። ወደ ሥራው ይሳባል፤ አንዱ የዐቢይ ምዕራፉን መለያ አይቶ ምሥጢሩን ያደንቃል፣ ዝምታ ይሰለጥንበታል፡፡ በልማድ መጽሐፍ ከመመልከት በልማድ ከመድገም ይከለከላል፡፡

አንዱ ደግሞ ሁሉንም አንድ አድርጎ ይሠራቸዋል፡፡ በዚህም ይሰለቻል፡፡ ዓለማዊ ሥራ ይሠራል፣ ለሐኬት ጽሙድ ሆኖ ይኖራል። አንዱ መጽሐፍ ከመመልከት ጥቂት ምሥጢር ያገኛል፡፡ በዚህም ትዕቢት ያድርበታል፡፡ በሰው መዘበት ያድርበታል፤ ይበድላል፡፡ አንዱ የልማድ ምክንያት ይሰለጥንበታል፣ አንዱም ይህን ሁሉ ድል ይነሣል፤ ከዚህ ሁሉ ይጠበቃል፡፡ ዕንቁ ክርስቶስን ገንዘብ እስኪያደርገው ወደኋላ አይመለስም፡፡ ደስ ብሎህ እግዚአብሔር ያዘዘውን የትሩፋት ሥራ ጀምር፡፡

#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ
"ኃጢአት ሲሠራ ባየኸው ወንድም ላይ አትፍረድ፥ አንተ ግልጽ የወጣ ኃጢአቱን እንጅ በስውር ለካህን የሚነግረውን ንስሐ አታውቅምና። ስለዚህ የራስህን ድካም ተመልከት።"

#ታላቁ_ቅዱስ_ባስልዮስ
"ብርሃን ወደ አንድ ቤት ውስጥ ሲገባ ጨለማን እንደሚያስወግድ ሁሉ፤ እግዚአብሔርን መፍራት ወደ አንድ ሰው ልብ ሲገባም አለማወቅን (በኃጢአት የሚወድቅባትን) ያስወግዳል።"

#አባ_እንጦንስ
እጅግ የተወደደና የተከበረው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ

“ወዳጄ ሆይ ወንድምህ ከአንተ ይልቅ አስተዋይና አዋቂ ብርቱም ቢሆን በዚህ ቅር አይበልህ ከዚህ ይልቅ እግዚአብሔርን አመስግን

ከወንድምህ አስተዋይነትና ብርታት ትጠቀማለህና በዚህ ሳታቆም ራስህን ስጦታየ ምንድነው?ወንድሜን እህቴን በምን ልጥቀም ?ብለህ ጠይቅ

ይህን ጥያቄ በትክክል ስትመልስ እንደመለስከው ምላሽም ስትተገብር በአንድ መልኩ በሚበልጥህ ሰው ቅር መሰኘትህን በሌላ መልኩ ደግሞ የምትበልጠውን ወንድምህን መናቅህን ታቆማለህ”
🌼እንኳን በሰላም መጣችሁ እህት ወንድሞችን 🌼
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዙሪያ ላላችሁ ጥያቄ መልስ የምታገኙበት እናንተም የምትጠየቁበት ማህበር ነው ።
👉በተጨማሪም ተከታታይ ትምህርቶች
👉ውይይቶች ይኖራሉ
በሚደረጉ ሐይማኖታዊ ውይይቶች ላይ
👉አንዱ የሌላውን እምነት ማናናቅ
👉የሌሎችን ፅሁፍ ቀድቶ መገልበጥ
👉...በጥብቅ የከለከለ ነው ።
🍀መልካም የውይይት ጊዜ🍀
Forwarded from ልባም ሴት 😍 (አላትዮን)
አንቺ ፀሐይ ሆይ የዛሬው ፈተና ልክ እንደደመና ተናፋቂ እንዲያደርግሽ እንጂ ፈፅማ የሚትጠፋ እንደማያደርግሽ አውቀሽ በተስፋ ኑሪ ።
አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሰዋል፤ ያበሰብሰዋልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ትምህርት በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ የተተረጎመ
ሰው ሁን!
1ኛ ነገ. ፪፥፫
አበባ አቤ
ከአባቶች አንዱ እንዲህ አለ
"አንበሳ ኃያልና አስፈሪ ነው ። መነኩሴው ተጋድሎውን ቢተው ፍላጎቱንም ቢከተል ግርማው ይጠፋል መዘባበቻም ይሆናል ። "

መፅሐፈ ገነት ገፅ 9
በዝቋላ ደብረ ከዋክብ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መነኮሳት አባቶች ላይ የተፈጸመውን የግፍ ግድያ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አውግዟል !

የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች የግፍ ግድያውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። መንግሥት ለቤተክርስቲያኗ እና ለዜጎች አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች ጠይቀዋል።

መንግሥት በቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ላይ የተፈጸመውን የግፍ ግድያ እንዲያጣራ እና የወንጀል ተግባሩን የፈጸሙትን ለሕግ እንዲያቀርብ እና የሕግ የበላይነትን እንዲያረጋግጥ ጠይቀዋል።

መንግሥት እየተፈጸሙ ያሉ እገታና የደኅንነት ሥጋቶችን በማስወገድ የዜጎችን የመንቀሳቀስ ሕገ መንግሥታዊ መብት የማስጠበቅ መንግሥታዊ እና ሕጋዊ ኀላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
2024/06/25 08:02:53
Back to Top
HTML Embed Code: